Monday, November 11, 2013

በፋሽስት ወያኔ ፕሮፓጋንዳ እየተወናበደ ያደገው የዛሬው የሃያዎቹ ዕድሜ ወጣት፡ ወያኔ ከገጠር ወደከተማ የገባ የገጠር ፈጣጣ ዱርዬ ቡድን መሆኑን አንብቦም ይሁን ከቀደምት ኢትዮጵያውያን እውነታውን መረዳትና እንዲሁም ከሚያየው ሁኔታ ማወቅና መገንዘብ ሲገባው፡ ዓይኑን በጨው እንዳጠበ ግለሰብ አይኔን ግምባር ያድርገው የወያኔ ፕሮፓጋንዳ ሰለባ ሆኖ ሃገሩን ለማዳን ከመሰለፍ ይልቅ፡ እራሱንም ሆነ ወገኑን፤ ሃገሪቱን እያጠፋ ካለው የፋሽስት ወያኔ መንጋ ጋር ወግኖ፤ ሃገሪቷን ጭለማ አድርጎ የ 3.5 ቢሊዮን ዶላር ሰራቂውን የመለስ ዘባንዳዊውን ምስል በየፌስቡክ ድህረ ገጽ ሰቅሎ የድርጎ ጉርሻ ንዋይ ከነዚሁ የገጠር ጎርፍ አመጣሽ ወያኔዎች እጅ ተቀብለው የሌባ ተቀባዮችን እያየን እውን እነዚህን ኢትዮጵያ አፈራችብን? ያስብላል።
ከሁሉ የሚገርመኝ ደግሞ፡ በየአረብ ሃገራት ተሰደው፡ ሌላው ቢቀር የወደፊት ሕይወታቸውን እንኳን ሊለውጥላቸው በማይችል ውጣ ውረድ ያሉ ወንድሞችና እህቶች፡ ለዚህ ሕይወት የዳረጋቸው የፋሽስት ወያኔ የዘረፋ ቡድን ጭካኔ መሆኑን ለማወቅ የተሳናቸው መሆኑን ነው። መለስ ዘባንዳዊውን የ3.5 ቢሊዮን ዶላር ባለቤት መሆኑን ያጋለጠው ሚዲያ ሚስጥርን ፈልፍሎ እውነታን በማጋለጥ የሚታወቀው በመዕራባውያን ክልል ሃገሮች ያለው " ዊክሊክስ " የሚባለው እውቅ ዓለም አቀፍ ሚዲያ ነው። ይህ የዘረፋ ገንዘብ በሃገራችን ውስጥ የልማት ተቋም ኖሮለት በየአረብ ሃገራትና በየቦታው የተሰደዱትን ኢትዮጵያውያን ሕይወት ሊለውጥ የሚችል ነበረ።
ሌላው ያስገረመኝ ደግሞ፡ ትናንት አባቶቻቸው በውትድርናው ዓለም እናት ኢትዮጵያ ሃገራችንን ሲጠብቁና ሲከላከሉ፡ አሁን ካሉት ከእንግዴ ልጆች ከነፋሽስት ወያኔ ጋር ሲፋለሙ ከነበሩ አብራክ የተፈጠሩ ወጣቶች፡ የመለስ ዘባንዳዊውን ፎቶግራፍ ሰቅለው ባለራእይ የሚል፡ ለአንድ ወንበዴ የማይገባው ቃል ጽፈው ስናይ፡ እንዴት እንደሚያቅለሸልሽ ጎበዝ? ጥቅምና እውነታ የተለያዩ ነገሮች ናቸው። አንዱ እንዲያውም የተቃውሞ መንፈስና ንግግሮች እየሰማሁ ነው ያደግሁት አልገባኝም ሲለኝ፡ ቢያንስ ቢያንስ ጀግናው አባቱ በጦር ሜዳ ያለፉት፡ ናዚውን የሻቢያ መንጋ ለመርዳት ምጽዋ ላይ ከትግራይ እንደግሪሳ ወረራ ካደረገው ጋር የፋሽስት ወያኔ ገበሬ ጦር ጋር ተፋልመው መውደቃቸው ስለኢትዮጵያ አንድነት ነው። ወያኔ ከገባ ጀምሮ 99% የሚሆነው ኢትዮጵያዊ ከትግራይ ተወላጆች በስተቀር አልተቀበለውም። አሁንም ሕወሃት ነው ጠቅላይ ሚንስትሩና የወከባ ሞተሩ። የደቡቡ ተወላጅ ደሳለኝ ኃይለማርያም የሕወሃት ቋሚ ሮቦት ስለመሆኑ ለማወቅ የግድ አስረጅ ሊኖር አይገባም። እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ስለፋሽስት ወያኔ ጠንቅቆ ያውቃል ፡ ሃገሩን የሚያፈቅር በምንም ዓይነት የወያኔ አጫዋችና የፕሮፓጋንዳ ሰለባ አይሆንም። መቃወም ብቻ ሳይሆን እነዚህን ነቀርሳ ወያኔዎችን ማስወገድና ኢትዮጵያን ከጭለማ ወደብርሃን የመለወጥ ኃላፊነቱ ማሰብና ማስተዋልን፤ ራስን አታልሎ ከፋሽስት ወያኔ ጉርሻ ገንዘብ በመቀበል በግድ የለሽነት ሳይሆን፡ ከፈጣሪ የተሰጠውን የማስተዋል ጸጋ በመጠቀም፡ ከራሴ በፊት ለኢትዮጵያ እናቴ፤ ወገኔ በማለት ነው።
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!!!!!!!!

No comments:

Post a Comment